"ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ" መዝ. 88፥3

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በቆቦ ወረዳ ዞብል የምትገኘው ራማ ኪዳነምሕረት አንድነት ገዳም

መግቢያ

የራማ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በቆቦ ወረዳ ዞብል አካባቢ ትገኛለች፡፡ ገዳሟ ቁጥራቸው ከዘጠኙ ቅዱሳን በሆኑት በአባ ጉባ እና በአባ ገሪማ በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከዛሬ 1,400 ዓመታት በፊት እንደተመሠረተች ታሪኳ ይነግረናል፡፡ በእነዚህ ቅዱሳን የተመሠረተችው ገዳም በ8ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ የተነሣችው ዮዲት ጉዲት (እሳቶ) እንዲሁም በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በግራኝ መሐመድ ተከታታይ ጥፋት ቢደርስባትም በልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ ሰማዕቷና ጻድቋ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ (እመ ምዑዝ) ዳግመኛ አቅንታ እንደገደመቻት ይነገራል፡፡ 

"እጅህን በምትጥልበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ስለዚህ በሥራህ ሁሉ ይባርክሃልና ፈጽመህ ስጠው፡፡" ዘዳግም. 15÷10

የገዳሟን የልማት እንቅስቃሴ ይደግፉ

የራማ ኪዳነምሕረት አንድነት ገዳም የተለያዩ ልማታዊ ሥራዎችን ለማከናወን በእንቅስቃሴ ላይ ትገኛለች፡፡ እነዚህ ልማታዊ ሥራዎች መከናወናቸው መናንያን በዓታቸውን አጽንተው እንዲኖሩ እና በገዳሟ የሚካሄዱት መንፈሳዊ አገልግሎቶች እንዳይቋረጡ ትልቅ እገዛ ያደርጋል፡፡ በገዳሟ ድጋፍ የሚፈልጉ ሥራዎች ውስጥ የሚከትሉት ይገኝበታል፡፡

  1. ገዳሟ ራሷን እንድትችል አንድ በጎ አድራጊ ምእመን በሰጡት ቦታ ላይ በደሴ ከተማ ግምቱ ክ80 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ጂ+7 (ባለ 7 ወለል) ሕንፃ በመሥራት ለማከራየት እንዲያስችል ተጀምሯል። በአሁኑ ወቅትም ሁለተኛው ወለል የተጠናቀቀ ሲሆን ሌላውን በመሥራት ማስፈጸም ይገባል።
  2. በገዳሟ የማገዶ እንጨት ስለሌለ ምግብ ማብሰል እንዲቻልና ያለውን የውሃ እጥረት ለመቅረፍ በሞተር ኃይል በመታገዝ የከርሰ ምድር ውሃ ማውጣት እንዲሁም የገዳሙ ወፍጮ ባለው የነዳጅ ዋጋ መናር ገቢው አነስተኛ ስለሆነ እነዚህን ሁሉ ለማከናወን የኤሌክትሪክ ኃይል ያስፈልጋል።
  3. የገዳሙ ዋና መተዳደሪያ የእርሻ (ግብርና) ሥራ ግብአቶችንና ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን ማሟላት ይጠበቃል፤
  4. በጓሮ አትክልት ልማት ላይ ለመሰማራት የባለሙያ እና የምርጥ ዘር እንዲሁም የመሳሪያ እርዳታ ያስፈልጋል፤
  5. በተግባረ ዕድ (እጅ ሥራ) ማለትም በሽመና፣ በሹራብ ሥራ ለመሰማራት ማሽንና ጥሬ ዕቃዎች (ክሮች እና የመሳሰሉት) ያስፈልጋሉ፤
  6. የገዳሟ አቀማመጥ በከብት እርባታ እና በከብት ማድለብ ለመሰማራት አመቺ ስለሆነ ለእርባታ የሚሆኑ ከብቶች አስፈላጊ ናቸው፤
  7. ሃገር በቀል ዛፎችን በመትከል በደን የተራቆተውን አካባቢ ለመሸፈን በአንጻሩም የማገዶን እጥረትን ለማቃለል ስለታሰበ ወቅቱን የጠበቀ የችግኝ አቅርቦት አስፈላጊ ነው፤
  8. በጅምር ላይ የሚገኘውን የአብነት ትምህርት ለማጠናከር ለመምህራኑ ደመወዝ እና ለተማሪዎች ቀለብ እንዲሆን የገንዘብ ድጋፍ ያስፈልጋል፡፡

ገዳሟን በገንዘብ ለመርዳት

  • ራማ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም፤
    የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ደሴ ቅርንጫፍ፤
    ሒሳብ ቁጥር- 1000142659224 ወይም
    የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ቆቦ ቅርንጫፍ –
    ሒሳብ ቁጥር – 1000037597426
  • ራማ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ፤
    አቢሲኒያ ባንክ፤ ጦቢያ ቅርንጫፍ፤
    አካውንት ቁጥር፤ 6973426