"እጅህን በምትጥልበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ስለዚህ በሥራህ ሁሉ ይባርክሃልና ፈጽመህ ስጠው፡፡" ዘዳግም. 15÷10

የበጎ አድራጊዎችን ድጋፍ የሚሹ የገዳሟ የልማት ዕቅዶች

ገዳም መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጥበት ብቻ ሳይሆን ልማት የሚከናወንበትም ሥፍራ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከሚሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት እና የተባሕትዎ ኑሮ በተጨማሪ ድንኳን በመስፋት ራሱን ያግዝ እንደነበር ሁሉ ገዳማትም ራሳቸውን ለማስተዳደር የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ያከናውናሉ፡፡


የራማ ኪዳነምሕረት ገዳም የተለያዩ ልማታዊ ሥራዎችን ለማናወን በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡ እነዚህ ልማታዊ ሥራዎች መሠራታቸው መናንናያን በዓታቸውን አጽንተው እንዲኖሩ እና በገዳሟ የሚካሄዱት መንፈሳዊ አገልግሎቶች እንዳይቋረጡ ትልቅ እገዛ ያደርጋል፡፡ በተለይም ገዳሟ ከተመጽዋችነት ተላቅቃ እና ራሷን ችላ በራሷ እንድትተዳደር ያስችላታል፡፡ በሌላም በኩል “ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ፤ በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ” የሚለው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ከአባቶች እግር ሥር የሚተኩ ልጆችን ለማፍራት በሥራ ላይ የሚገኘውን የአብነት ትምህርት ቋሚና ዘላቂ በሆነ መልኩ ማጠናከር አስፈላጊ ነው፡፡ በመሆኑም ገዳሟ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የልማት ሥራዎችን ለማከናወን የሕዝበ ክርስቲያኑን ድጋፍ ትሻለች፡፡


  1. ገዳሟ ራሷን እንድትችል አንድ በጎ አድራጊ ምእመን በሰጡት ቦታ ላይ በደሴ ከተማ ግምቱ ክ80 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ጂ+7 (ባለ 7 ወለል) ሕንፃ በመሥራት ለማከራየት እንዲያስችል ተጀምሯል። በአሁኑ ወቅትም ሁለተኛው ወለል የተጠናቀቀ ሲሆን ሌላውን በመሥራት ማስፈጸም ይገባል፤
  2. በገዳሟ የማገዶ እንጨት ስለሌለ ምግብ ማብሰል እንዲቻልና ያለውን የውሃ እጥረት ለመቅረፍ በሞተር ኃይል በመታገዝ የከርሰ ምድር ውሃ ማውጣት እንዲሁም የገዳሙ ወፍጮ ባለው የነዳጅ ዋጋ መናር ገቢው አነስተኛ ስለሆነ እነዚህን ሁሉ ለማከናወን የኤሌክትሪክ ኃይል ያስፈልጋል፤
  3. የገዳሙ ዋና መተዳደሪያ የእርሻ (ግብርና) ሥራ ግብአቶችንና ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን ማሟላት ይጠበቃል፤
  4. በጓሮ አትክልት ልማት ላይ ለመሰማራት የባለሙያ እና የምርጥ ዘር እንዲሁም የመሳሪያ እርዳታ ያስፈልጋል
  5. በተግባረ ዕድ (እጅ ሥራ) ማለትም በሽመና፣ በሹራብ ሥራ ለመሰማራት ማሽንና ጥሬ ዕቃዎች (ክሮች እና የመሳሰሉት ያስፈልጋሉ፤
  6. የገዳሟ አቀማመጥ በከብት እርባታ እና በከብት ማድለብ ለመሰማራት አመቺ ስለሆነ ለእርባታ የሚሆኑ ከብቶች አስፈላጊ ናቸው፤
  7. ሃገር በቀል ዛፎችን በመትከል በደን የተራቆተውን አካባቢ ለመሸፈን በአንጻሩም የማገዶን እጥረትን ለማቃለል ስለታሰበ ወቅቱን የጠበቀ የችግኝ አቅርቦት አስፈላጊ ነው፤
  8. በጅምር ላይ የሚገኘውን የአብነት ትምህርት ለማጠናከር ለመምህራኑ ደመወዝ እና ለተማሪዎች ቀለብ እንዲሆን የገንዘብ ድጋፍ ያስፈልጋል፡፡

የተከበራችሁ በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ የገዳሟ ወዳጆች ኢትዮጵያውያውን ምእመናንና ምእመናት ከላይ የተዘረዘሩትን ሥራዎች ለማከናወን “ጥርስና ከንፈር ቢተባበር ያምር” ፣ “ሣሮች ቢሰባሰቡ የቤት ክዳን ይሆናሉ” እንዳሉ አበው ተባብረን ይህን ሥራ እንድንሠራ በራማ ኪዳነምሕረት ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የልማት ኮሚቴ አስተባባሪዎች

  1. ቆሞስ አባ ጥዑመልሣን ብርሃኑ — የገዳሟ አበምኔት 
     ስልክ ቁጥር፡- +251911025881/+251936993302
  1. ቀሲስ ሳምሶን በቀለ —- የአዲስ አበባ የገዳሟ መርጃ ማኅበር ሰብሳቢ
    ስልክ ቁጥር ፡- +251911639820
  1. አቶ ዳኛቸው ዓለሙ  የደሴ የገዳሟ መርጃ ማኅበር ሰብሳቢ
    ስልክ ቁጥር ፡- +251914714220
  1. አቶ ተክሌ ገብረ ዮሐንስ   —— – የቆቦ የገዳሟ መርጃ ማኅበር ሰብሳቢ
    ስልክ ቁጥር ፡- +251974382497

የገንዘብ ድጋፍ ለምታደርጉ

  1. ራማ ኪዳነምሕረት አንድነት ገዳም
    አቢሲኒያ ባንክ፤ ጦቢያ ቅርንጫፍ
    አካውንት ቁጥር፡- 6973426
  1. የራማ ቅድስት ኪዳነምሕረት አንድነት ገዳም
    የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
    አካውንት ቁጥር፡- 1000142659224