"እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።' 2ቆሮ. 9፥6-7

በደሴ ከተማ የገዳሟ ቋሚ ገቢ ማስገኛ ባለ ሰባት ወለል ሕንፃ ግንባታ​

የራማ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ቁጥራቸው ከ200 በላይ መነኮሳት እና መነኮሳዪያት እንዲሁም ከ300 በላይ የአብነት ተማሪዎች ይገኛሉ፡፡ የገዳሟ አብዛኛው መተዳደሪያ ግብርና ሲሆን እርሱም በአካባቢው ሁልጊዜ በሚከሰተው የዝናም እጥረት ምክንያት ከእጅ ወደ አፍ ነው፡፡ በመሆኑም ገዳሟን ከተረጂነት ለማላቀቅ አንድ በጎ አድራጊ ሰው በደሴ ከተማ ላይ ለገዳሟ በሰጡት መሬት ላይ ባለ ሰባት ፎቅ ሕንፃ በመሥራት ለማከራየት እንቅስቃሴው የተጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የሕንፃ ግንባታው የመጀመሪያው ወለል በሙሉ እና የሁለተኛው ወለል ኮለሞች ተጠናቅቀዋል፡፡ በመሆኑም በሀገር ውስጥ እና በውጪ የምትገኙ የገዳሟ ወዳጆች በሙሉ ለሚገነባው የገዳሟ ቋሚ ገቢ ማስገኛ ሕንፃ በገንዘብ እና በግንባታ ቁሳቁስ የእርዳታ እጃችሁን እንድትዘረጉ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ ለግንባታው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ዝርዝር በቀጣዩ ሰንጠርዥ ላይ ይመልከቱ፡፡

የቁሳቁሱ ዓይነትብዛትየቁሳቁሱ ዓይነት  ብዛት
የተለያየ መጠን ያላቸው ብረቶች (ባለ 10፣12፣14፣16 እና 20) 9953ጠጠር45 መኪና
ባለ 30 ጣውላ275አሸዋ40 መኪና
ምስማር110 ካርቶን ሪጂድ የኤሌክትሪክ ኮንዲት
(ባለ 16)
750
ብላክ ዋየር400 ኪ.ግሳኒተሪ ፒቪሲ
(ባለ 110)
125
ዳንጎቴ ሲሚንቶ2400 ኩንታልባለ 75115
  ባለ 50115

"እጅህን በምትጥልበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ስለዚህ በሥራህ ሁሉ ይባርክሃልና ፈጽመህ ስጠው፡፡" ዘዳግም. 15÷10

ለገዳሟ መርጃ ሕንፃ ግንባታ የዕርዳታ ቃል መግቢያ

ቃል መግቢያ ቅጹን ከሞሉ በኋላ ቆርጠው ለገዳሟ መርጃ ኰሚቴ አባላት መመለስዎን አይርሱ፡፡

በቁሳቁስ

በገንዘብ ለመርዳት

  • ራማ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም፤
    የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ደሴ ቅርንጫፍ፤
    ሒሳብ ቁጥር- 1000142659224 ወይም
    የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ቆቦ ቅርንጫፍ –
    ሒሳብ ቁጥር – 1000037597426
  • ራማ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ፤
    አቢሲኒያ ባንክ፤ ጦቢያ ቅርንጫፍ፤
    አካውንት ቁጥር፤ 6973426
IMG_20230715_155252_090